loading
ኬንያ ውስጥ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ በሄሊኮፕተር አደጋ ሰባት አሜሪካዊያን ሞቱ፡፡

ኬንያ ውስጥ ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ በሄሊኮፕተር አደጋ ሰባት አሜሪካዊያን ሞቱ፡፡

አራት አሜሪካዊያንን አሳፍሮ ይበር የነበረ ሄሊኮፕተር ቱርካና ሀይቅ ላይ በሚገኝ ደሴት ላይ ተከስክሶ ኬንያዊውን አብራሪ ጨምሮ ሁሉም መሞታቸውን የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ተናግረዋል፡፡

በደሴቷ ከሚገኘው ብሄራዊ ፓርክ ትናንት አመሻሽ ላይ ሁለት ሄሊኮፕተሮች በረራ አድርገው አንዱ ብዙም ሳይጓዝ አደጋ እንደደረሰበት የኬንያ ሲቪል አቬሽን ባለስንጣን ገልጿል፡፡

ናይሮቢ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ አራት ዜጎቹ በአደጋው ሳቢያ መሞታቸውን ማረጋገጫ ሰጥቷል ነው የተባለው፡፡

አሶሸትድ ፕሬስ እንደዘገበው ባለፈው ወር በተመሳሳይ አደጋ ሶስት አሜሪካዊያን ህይዎታቸው አልፏል፡፡ ይህም አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አሜሪካ ሰባት ዜጎቿን በአደጋ እንድታጣ አድርጓታል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *