loading
ካጋሜ አዲሶቹ የፓርላማ አባላት የሩዋንዳን ሉዓላዊነት እንዲያስከብሩ አደራ ብለዋል

አርትስ 11/1/2011
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ጋካሜ በቅርቡ ተሾመው ቃለ መሃላ የፈጸሙ የምክር ቤት አባላት መንግስት በተጠያቂነት እንዲሰራ እንዲታገሉና፣ እንዲሁም ሙስናና ከፋፋይ ፖለቲካን አጥብቀው እንዲዋጉ አሳስበዋል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ለዓምስት ዓመታት ለማገልገል የተመረጡትን የህግ አውጭ አባላት ወደ ህዝባችሁ ቀርባችሁ በመስራት በቅስቀሳ ወቅት የገባችሁትን ቃል ሳትሸራርፉ መፈጸማችሁን እንዳትረሱ ብለዋቸዋል፡፡
አዲሱ የሩዋንዳ ፓርላማ የአካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሴቶችና ወጣቶችን እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወንበር ያገኙበት በመሆኑ አድናቆት ተችሮታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *