loading
ካይሮ የመጀመሪያዋን ሴት የኮፕቲክ ክርስቲያን በአስተዳዳሪነት ሾመች፡፡

ግብጽ የኮፕቲክ ክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑትን ይህችን ሴት ወደ ስልጣን ስታመጣ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
የ 51 ዓመቷ ማናል አዋድ ሚካኤል የጊዛ ምክትል አስተዳዳሪ ሆነው ሲሾሙ በፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ፊት ቆመው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
ኢጂፕሽያን ስትሪትስ እንደዘገበው ሚካኤል ከክርስትና እምነት ተከታዮች የመጀመሪያዋ፣ ከግብጻዊያን ሴቶች ደግሞ ከናዲያ አህመድ ቀጥለው ሁለተኛዋ ሴት አስተዳዳሪ ሆነው በመመረጥ አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡
አዲሷ አስተዳዳሪ በተፈጥሮ ሳይንስ ከአሌክሳንደሪያ ዩንቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ምሩቅ ሲሆኑ ላለፉት 20 ዓመታት በሙያቸው በተለያዩ ሀላፊነቶች ሀገራቸውን አገልግለዋል ተብሏል፡፡

አርትስ 25/12/2010

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *