ካይሮ ሶስት ፖ ሊ ሶችን በ15ዓመት እስር ቀጣች
አርትስ 12/04/2011
የግብጽ ፍርድ ቤት ካይሮ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተመድበው በሚሰሩ ሶስት የፖሊስ አባላትና በሌሎች አራት የአየር መንገዱ ሰራተኞች ላይ ነው ቅጣቱን ያስተላለፈው፡፡
ግለሰቦቹ ጥፋተኛ የተባሉት ከህገ ወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪወች ጉቦ በመቀበል ሳይፈተሸ እንዲተላለፉ በማድረግ ወንጀል ተከሰው ነው፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ ምርመራውን ከጀመረና ማስረጃወችን ካቀረበባቸው በኋላ ጥፋታቸውን አምነው የፈፀሙትን ወንጀል ሁሉ በዝርዝር ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በኋላም ወደ ካይሮ የወንጀል ፍርድ ቤት እንዲተላለፉ ተደርጎ የፍርደደ ሂደታቸውን ሲከታሉ ቆይተው ሰባቱም ተከሳሾቸች በ15 ዓመት እስራ እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፡
ተከሳሾቹ በተለይ ከአንድ በህጋዊ መንገድ የውጭ ምንዛሬ ስራ ላይ ከተሰማራ ነጋዴ ጋር በመመሳጠር በርካታ ገንዘብ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር እንዲወጣ አድረገዋል ብሏል ፍርድ ቤቱ፡፡