loading
ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ በቁጥጥር ስር ዋለ

ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ በቁጥጥር ስር ዋለ
በድሬደዋ ከተማ እና ያቤሎ አካባቢ በድምሩ 2 ሚሊዮን  505 ሺህ ,225 ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ግምታዊ ዋጋው 1,ሚሊዮን 300 ሺህ ብር የሆነ ኮንትሮባንድ ልባሽ ጨርቅና ሲጋራ የካቲት 22/2011 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት  ድሬደዋ ውስጥ አዲሱ ኬላ ተብሎ የሚጠራ ሰፈር በቁጥጥር ስር ውሏል።
የድሬደዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው ኮንትሮባንዱ መጋዘን ውስጥ ተከማችቶ እያለ ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ ሊያዝ ችሏል።
በተመሳሳይ ግምታዊ ዋጋው 1ሚሊዮን ,205 ሺህ ,225 ብር የሆነ የኮንትሮባንድ ንግድ ውስጥ የተገኙ አልባሳትና ኤሌክትሮኒክስ ምርቶች የካቲት 22/2011 ዓ.ም ያቤሎ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ዉሏል።
ከገቢዎች ሚኒስቴር እንዳገኘነዉ መረጃ የኮንትሮባንድ ዕቃው በሰሌዳ ቁጥር 47799 ኦሮ ተሽከርካሪ ሲጓጓዝ በፀጥታ ሃይሎች ተይዟል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *