loading
ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 25፣2013 ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
የሲዳማ ክልል ፖሊስ  ኮሚሽነር አበራ አሬራ ለኢዜአ እንደገለጹት፤  ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት  እጅ ከፍንጅ ተይዘው ነው። ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በተካሄደ አሰሳ በሃዋሳ ከተማ በጥቁር ገበያ ለማዘዋወር ታቅዶ የነበረና የህትመት ሂደቱ ያላለቀ ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን ነው ኮሚሽነሩ ያስታወቁት፡፡

በዚህ የወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው  ጉዳያቸውን ለማጣራት ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። ከጉዳዩ ጋር ግኙነት አላቸው የተባሉ ሌሎች ተጠርጠሪዎችን ይዞመለህ ለማቅረብ ም  ክትትል እየተደረገ  ነው ተብሏል፡፡ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች በሆቴል ውስጥ የሚያትሙትን ሀሰተኛ ዶላር የሚገዛ ሰው ሲያፈላልጉ እንደነበር ያመለከቱት ኮሚሽነሩ፤ የህብረተሰቡና የሆቴል ባለቤቶቹ ጥቆማ ለግለሰቦቹ መያዝ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሰዋል።

የሲዳማ ክልል ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያገናኘውን ዋና መንገድ አቋርጦ የሚያልፍ በመሆኑ ለሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና ገንዘብ ዝውውር እንዲሁም ለኮንትሮባንድ ንግድ የተጋለጠ ነው ሲሉም ኮሚሽነር አበራ ገልጸዋል። ወንጀልን በጋራ ለመከላከል ህብረተሰቡ ለፖሊስ እየሰጠ ያለውን መረጃና ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *