loading
ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ ቦቲ መኪና ህገ ወጥ መሣሪያ ጭኖ ሲጓዝ በህግ ቁጥጥር ስር ዋለ

አርትስ 10/02/2011

ሰሞኑን ከሱዳን ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበረ ቤንዚን የጫነ ቦቲ መኪና ኮድ -3 87297 የፊቱ ተሳቢ ኮድ -3 27172 ኢት የሆነ ህገ ወጥ መሣሪያ ጭኖ ሲጓጓዝ ለጎንደር ጉምሩክ ቅርጫፍ ጽ/ቤት በደረሠ ጥቆማ በህግ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የተያዘው የመሣሪያ ብዛትም ሽጉጥ 999/ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ/ ሲሆን የክላሽ ጠመንጃ ብዛት 30/ሠላሣ/ በመዳበሪያ ተጠቅሎ ከነዳጁ ጋር ተጭኖ መገኘቱን የጎንደር ጉምሩክ አስተውቋል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃም እሽከርካሪውና ረዳቱ በህግ ስር ተይዘው የሚገኙ ሲሆን የመኪናው ባለቤት ግን መቅረብ አለመቻሉን ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *