loading
እስራኤል እና ሩሲያ በሶሪያ ቀውስ ዙሪያ መምከራቸው ተሰማ

እስራኤል እና ሩሲያ በሶሪያ ቀውስ ዙሪያ መምከራቸው ተሰማ፡፡

 

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከሩሲያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሶሪያ ጉዳዮች ልዩ ተወካይ አሌክሳንደር ላቭሬንቲቭ ጋር እየሩሳሌም በሚገኘው የጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ተወያይተዋል፡፡

 

በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት በቀጣይ በሶሪያ ባለው ቀውስ መፍትሄ ዙሪያ ላይ የመከሩ ሲሆን፤  በተለይም ኢራን በሶሪያ ጉዳይ ያላትን ጣልቃገብነት የተለየ ትኩረት ሰጥተው ምክክር ማድረጋቸውን የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግሯል፡፡

በቀጣይም የወታደራዊ ደህንነት ስርዓቱን በማጠናከር የእርስ በርስ ግጭቶችን ለመፍታት እንደሚሰሩም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ አዲስ አመት መግቢያ ላይ በሶሪያ ያላቸውን ወታደራዊ ሃይል በጣምራ ለመምራት መስማማታቸውን ተከትሎ ነው የአሁኑ ውይይት የተካሄደው፡፡

እስራኤል በሶሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ወታደራዊ ሀይል መውጣቱን ተከትሎ የኢራን ወታደሮች ሊጠናከሩ ይችላሉ በሚል ስጋት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥታለች፡፡

እ.አ.አ በ2015 ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ወታደሯን ወደ ሶሪያ መላኳ ይታወሳል፡፡ እስራኤል ባለፉት አመታት  በሶሪያ የሚገኙ የኢራን ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠሩ የአየር ጥቃቶችን መፈጸሟን የቻይና ዜና አገልግሎት ሽኑዋ ዘግቧል፡፡

 

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *