loading
ኤርባስ ኤ 380 የተሰኘውን አውሮፕላን ማምረት አላዋጣኝም አለ፡፡

ኤርባስ ኤ 380 የተሰኘውን አውሮፕላን ማምረት አላዋጣኝም አለ፡፡

በአውሮፓ ትልቁ አውሮፕላን አምራች ኤር ባስ ኩባንያ በፈረንጆቹ 2021 ሱፐር ጃምቦ ጀት የመንገደኞች አውሮፕላን ማምረቱን ለማቆም ማሰቡን ይፋ አድርጓል፡፡

ኤር ባስ ምርቱን ለማቆም የተገደድኩት ገበያው ስለተቀዛቀዘ ነው ማለቱን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡

ኤር ባስ ይህን አውሮፕላን ማምረት የጀመረው ከቦይንግ 747 ጋር በመፎካከር የገበያ ድርሻውን ለመቆጣጠር ቢሆንም አብዛኞቹ አየር መንገዶች ቀላል የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ምርጫቸው በማድረጋቸው እንዳሰበው አልሆነለትም፡፡

ኩባንውያ በመግለጫው እንዳስታወቀው ዋናው የገበያው የጀርባ አጥንት የሆነው የኤሜሬቶች አየር መንገድ ይህን አውሮፕላን ለመግዛት ትእዛዝ መቀነሱ ምርቱን ለማቆም አንዱ ምክንያት ነው፡፡

የኩባንያው ደንበኛ የሆነው ኤሬቶች አየር መንገድ ሊቀ መንበር ሸይክ ሰይድ አል መክቱም ደንበኝነታችን መቋረጡ ቢያሳዝነንም ሁኔታዎች ባለመፍቀዳቸው ነው ይህን ያደረግንው ብለዋል፡፡

ኩባንያው ስራውን ከማቆሙ በፊት ከ3 ሺህ እስከ 3 ሺህ 500 በሚሆኑ ሰራተኞቹ እጣ ፋንታ ዙሪያ ለመምከር በቀጣዩ ሳምንት ቀጠሮ ይዟል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *