loading
ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ተፈራርመውታል፡፡ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ኪቪድ19ኝን ጨምሮ በጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግና ለህክምና ቁሳቁስ መግዣ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

ሁለቱን የከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በማቅረብ የጤና ስርአቱን ለማዘመን ለሚደረገው ጥረት ይውላልም ነው የተባለው፡፡በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ድጋፉ በኢትዮጵያ ኮቪድ19ኝን ጨምሮ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት እንደሚውል ተናግረዋል፡፡አሁን የተደረገው ድጋፍም የሁለቱን ሃገራት ወዳጅነት እንደሚያጠናክር መናገራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *