ኢትዮጵያ እና ኬኒያ በድንበር አካባቢ በሚፈጠሩ ግጭቶችና መከላከያ መንገዶቻቸው ላይ መከሩ
ኢትዮጵያ እና ኬኒያ በድንበር አካባቢ በሚፈጠሩ ግጭቶችና መከላከያ መንገዶቻቸው ላይ መከሩ
አርትስ 05/04/2011
በሃዋሳ ከተማ በተካሄደውና በኢትዮጵያ እና በኬንያ ወሰን አካባቢ ከጋራ ሃብት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት በመከረው በዚሁ መድረክ ላይ ሃገራቱ ችግሮችን በመፍታት ዘላቂ ሰላም ማስፈን አለባቸው ተብሏል።
በዚሁ በሁለቱ ሃገራት የወሰን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የተካሄደ ምክክር ላይ ከሁለቱ ሀገራት የተወከሉ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘይኑ ጀማል እንደገለጹት የኢትዮጵያና የኬኒያ መልካም ጉርብትና በአፍሪካ በአርዓያነት የሚጠቀስ ነው ።
አልፎ አልፎ በሁለቱ ሀገራት ወሰን አካባቢ ከሃብት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚነሱ የተለመዱ ግጭቶች መኖራቸውን እና የውይይት መድረኩ ችግሮችን እንደ ባህላዊ የግጭት መፍቻ መንገዶች ባሉ ዘዴዎች ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከሩን ተናግረዋል።
ለዚህም ቀደም ሲል በደቡብ ኦሞና ቱርካና ሃይቅ፣ በኢትዮጵያና ኬኒያ ሁለቱም ሞያሌዎች አካባቢ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦችን ያሳተፉ ተመሳሳይ ውይይቶች ሲካሄዱ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡