ኢትዮጵያ አየር ላይ ያለ እርጥበትን ወደ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚቀይረውን ቴክኖሎጂ ከህንድ ለመዉሰድ ዝግጅት እያደረኩ ነዉ አለች
አርትስ 20/03/2011
ቴክኖሎጂዉን ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እና በኢትዮጵያ የህንድአምባሳደር አኑራግ ስሪቫስታቫ ተወያይተዋል፡፡
በዉይታቸዉ ወቅትም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደፊት በሚያራምዱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ በትኩረትእየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ህንድ በተለይ አየር ላይ ያለ እርጥበትን ወደ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚቀይር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ውሃ ታገኛለች፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በድረገጹ እንዳስታወቀዉ ፤ከህንድ የቴክኖሎጂ ዉጤት ኢትዮጵያ ልምድ እንድትቀስምም በ2011 ዓ.ም ሚያዝያ ወርላይ የህንድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢግዚቢሽን በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከህንድ ኢንባሲ ጋር በመተባበር በህንድ የጎላ ጠቀሜታ ያላቸውን የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ዉጤቶች ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ የሚያካሄዱት ፡፡