ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስን እንድታስተናግድ ተመረጠች፡፡
ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስን እንድታስተናግድ ተመረጠች፡፡
ኮንፈረንሱ 2ሺ 5መቶ ሰዎችና 90 ሚኒስትሮች ይሳተፉበታል ብለዋል፡፡
አለም አቀፉ የቴሌኮም ህብረት የኢትዮጵያን የቴሌኮም ዘርፍ ወደ ግል ለማዞር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የህብረቱ ዋና ፀሃፊ ሆውሊን ዛሆ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ጋር መክረዋል፡፡
ዋና ፀሃፊው በቴሌኮም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የአፍሪካ ቢሯቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመክፈት እቅድ እንዳላቸውም ዋና ፀሃፊው ሆውሊን ዛሆ ተናግረዋል፡፡
ሃላፊው ኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፉን ለማሳደግ እየሰራች ያለውን ስራ እና ሴቶችን በቴክኖሎጂ መስክ ለማሳተፍ የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡