ኢትዮጵያ ነገ አዲስ ፕሬዚዳንት ይኖራታል
አርትስ 14/02/2011
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ነገ ሁለተኛ ልዩ ስብሰባቸውን ያካሂዳሉ። በስብሰባውም አዲስ የሪፐብሊኩን ፕሬዚዳንት እንደሚሾሙ ይጠበቃል፡፡
ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ምክር ቤቶቹ አዲሱን ሹመት የሚያካሂዱት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመየሚያቀርቡትን መልቀቂያ በመቀበል ነው።
ለፕሬዚዳንትንት ስልጣን የታጨው ማን እንደሆነ እስካሁን ፍንጭ አልተሰጠም።