loading
ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና አርትስ ቴሌቪዥን ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና አርትስ ቴሌቪዥን ተፈራረሙ

የበርካታ ደጋፊዎች ባለቤት መሆኑ የሚታወቀው ኢትዮጵያ ቡና፤ ቡናችን የተሰኘውን የቴሌቪዥን ፕሮግራሙን በአርትስ ቴሌቪዥን ለማስተላለፍ ከቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር በዛሬው ዕለት ይፋዊ ስምምነት ፈፅሟል፡፡

ስምምነቱን በአርትስ በኩል ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል እና የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ በቀለ ፈርመዋል፡፡

አቶ ያሬድ ከስምምነቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ አርትስ በቅርብ ጊዜ መቋቋሙን ፤አዲስ አበባ እና አሜሪካ ቺካጎ ላይ መቋቋሙን ተናግረው፤ በኢትዮጵያና አፍሪካ ሕዳሴ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

ጣቢያው ከቴሌቪዥን ባለፈ በኦንላይን ሚዲያውም ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቡናም የአርትስ አጋር መሆኑ እንዳስደሰታቸው ተናግረው፤ ከበርካታ ውይይቶች በኋላ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

ክለቡ ትልቅ ድጋፍ አለው፤ አርትስም ስፖርቱን መደገፍ ዋና ዓላማው መሆኑን አቶ ያሬድ ገልፀዋል:: ዋና ስራ አስፈፃሚው በሌሎችም ስፖርቶች ላይ አርትስ ትኩረት እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡

አቶ ስንታየሁ በክለቡ የአርባ ዓመታት የተሻገረ ታሪክ ውስጥ የተለያዩ አዳዲስ ተግባራት እንደተከናወነና ቀደም ብሎ የጀመረው የሬዲዮ ፕሮግራም እየተጠናከረ መምጣቱን፤ የቲቪ ፕሮግራሙም ቢሆን አስቀድመው መጀመራቸውን አስታውሰዋል፡፡

የቴሌቪዥን ጣቢያው  የያዛቸውን ራዕይ በመመልከት በርካታ አማራጮችን ካጤኑ በኋላ ወደ አርትስ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

ስራ አስኪያጁ ክለቡ በተለያዩ ዓለማት ያለውን ድጋፍ ለማጠናከር፤ የአርትስ ስርጭትም ይህንን የሚያሟላ በመሆኑ ከአርትስ ቴሌቪዥን ጋር ተስማምተናል ብለዋል፡፡ ወደፊትም የተሻለ ስራ አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

ስምምነቱም ለአንድ ዓመት ያህል የሚዘልቅ ይሆናል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *