loading
ኢትዮጵያ በቀጣይ 30 ዓመታት የሚኖራትን የህዝብ ቁጥር እድገት በልማት ዕቅዷ ማጤን አንደሚኖርባት ምሁራን ገለጹ፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 ኢትዮጵያ በቀጣይ 30 ዓመታት የሚኖራትን የህዝብ ቁጥር እድገት በልማት ዕቅዷ ማጤን አንደሚኖርባት ምሁራን ገለጹ፡፡ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 30 ዓመታት የሚኖራትን የህዝብ ቁጥር እድገት በምትቀርጻቸው የልማት ዕቅዶች ታሳቢ እንድታደርግ ምሁራን ሀሳብ አቅርበዋል፡፡”ባለሰማያዊ አርማ የተሰኘ” የኢትዮጵያን 2050 ተግዳሮቶችና እድሎችን የሚዳስስ ሪፖርትን አስመልክቶ በበይነ መረብ በመታገዝ መግለጫ ተሰጥቷል።

ሪፖርቱ በአገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን የተዘጋጀ ሲሆን በከተማ ልማት፣ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ፣ ግብርና፣ ስነ-ህዝብ፣ ምጣኔ ሃብትና ሌሎች የሙያ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው።ፈጣን የከተሞችና የምጣኔ ሃብት እድገት፣ የጾታ እኩልነትን ጨምሮ አሥር የትኩረት አቅጣጫዎች እንዲሁም አምስት ዋና ዋና የእስትራቴጂ እርምጃዎችን ሪፖርቱ ማካተቱ ተገልጿል።

የኢትዮጵያን እድገትና ልማት በተመለከተ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው የህዝብ ብዛትና የማህበራዊ ምጣኔ ሃብት ክንውን ውጤት አለመመጣጠን የሪፖርቱ ዋና ማጠንጠኛ መሆኑም ነው የተመላከተው።በመግለጫው የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር በቀጣዮቹ ሦስት አስርት ዓመታት 200 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ሪፖርቱ ግምት ማስቀመጡም ተገልጿል።በእዚህም የሚቀረጹ የልማት ዕቅዶች ይህን የህዝብ ቁጥር እድገት ታሳቢ ማድረገ እንዳለባቸው ምሁራኑ መክረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *