loading
ኢትዮጵያና ቱርክ በባህልና በቅርስ ጥበቃ ዘርፍ በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ

ኢትዮጵያና ቱርክ በባህልና በቅርስ ጥበቃ ዘርፍ በትብብር እንደሚሰሩ ተገለጸ

ይህ የተባለው በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳሁን የተመራ የልዑካን ቡድን ከቱርክ ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ሰርዳር ካም ጋር አንካራ ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡

ሁለቱ አገራት በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ትብብራቸውን ይበልጥ በማጠናከር ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅት ዶ/ር ሂሩት የቱርክ የትብብር ኤጀንሲ በኢትዮጵያ በቅርስነት ተመዝግበው የሚገኙትን የአልነጃሺን መስጊድ እና ሐረር የሚገኘውን ጥንታዊ የኦቶማን ቱርክ ቆንስላ ጽ/ቤት ለማደስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ቱርክ በኤምባሲ ደረጃ በአፍሪካ ከሰሃራ በታች የመጀመሪያ የሆነውን በአዲስ አበባ በ1918 ዓ.ም መክፈቷ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ደግሞ ኤምባሲዋን በ1925 ዓ.ም  በቱርክ አንካራ ላይ ከፍታለች።

ሀገራቱ  የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት በ1888 ዓ.ም ጥንታዊ የኦቶማን ቱርክ መንግስት የመጀመሪያውን ቆንስላ ጽ/ቤት ሐረር ላይ ከመሰረተበት ጊዜ በኋላ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *