loading
ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ያለው ለውጥ የሚደነቅ ነው አሉ

አርትስ 01/13/2010
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ይህን ያሉት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሸሙትን አሊ ሱለይማንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነገሩበት ወቅት ነው፡፡
አምባሳደር አሊ ሱለይማን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንቱ ባቀረቡበት ወቅት ማክሮን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያላቸውን ክብርና አድናቆት እንዲያደርሱላቸው ነግረዋቸዋል፡፡
የፕሬዝዳንቱ አድናቆት የመነጨው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እየታዩ ካሉት ወቅታዊ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጦች ነው፡፡
ማክሮን በመጭው ጥቅምት ወር ከዶክተር አብይ ጋር ተገናኝተው የመወያየት ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል::
ኤፍ.ቢ.ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *