ኢህአዴግ አጋር ፖርቲዎችን ወደ ፓርቲነት ለማምጣት ጥናቱ እንዲጠናቀቅና ድርጅቱ የሁሉም እንዲሆን ይሰራል አሉ የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
አርትስ 23/01/2011
በ11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ኢህአዴግ በ10ኛው ጉባዔ ከተወሰኑ ውሳኔዎች መካከል የድርጅቱን አጋር ፓርቲዎች ወደ ፓርቲነት ለማምጣት ጥናት እንዲደረግ የሚለው ቢገኝበትም አገሪቱ ወስጥ በነበረው ችግር ምክንያት ለዚህ ጉባዔ አለመቅረቡን የተናገሩት ጠ/ሚኒስትሩ ተጠንቶ እንደሚወሰን ተናግረዋል። አጋር ፓርቲዎችም በድጋፍ ንግግራቸው ጠቅሰውታል።
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የተጀመረው 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት የድርጅቱ ህገ ደንብ በሚያዘው መሰረት ከ2ዓመት ስከ 2ዓመት ተኩል መካሄድ ያለበት ሲሆን ባለፈው መጋቢት ላይ መተላለፉ ይታወሳል።
ድርጅቱ ለ20አገራት የፖለቲካ ተወካዮች ጥሪ አቅርቦ የዘጠኝ አገራት ተወካዮች ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።