loading
ኡሁሩ ኬንያታ ደቡብ ሱዳኖችን አድንቀዋል፡፡

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ይበል የሚያሰኝ ሲሉ አሞካሽተውታል፡፡
በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች ከጦርነት ይልቅ ሰላምን እንደ አማራጭ መውሰዳቸው ብልህነት ነው ያሉት ኬንያታ ሀገራቸው ይሄን የተቀደሰ ሀሳብ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡
ሱዳን ካርቱም ላይ የተደረገው ስምምነት የፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የቀድሞው ምክትላቸውና የአሁኑ ተቀናነቃኛቸው ዶክተር ሪክ ማቻር ወደ ሀገር ቤት ገብተው በቀድሞ ስራቸው እንዲቀጥሉ የሚያደርግ ነው፡፡ የኬንያው ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችም የስምምነቱ አካል ናቸው፡፡ ደቡብ ሱዳን ራሷን ችላ ሀገር በሆነች ማግስት ጀምረው ጎራ ለይተው ሲታኮሱ የነበሩት እነዚህ ተፋላሚ ሀይሎች ባደረጉት ስምምነት መሰረት ተቃዋሚዎቹ ያነሱት የስልጣን መጋራት ጥያቄ መልስ አግኝቷል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *