አዲስ ወግ ዌቢናር ለሁለተኛ ግዜ ፈጠራ በቀውስ ጊዜ በሚል ርእስ ውይይት እያደረገ ነዉ፡፡
አዲስ ወግ ዌቢናር ለሁለተኛ ግዜ ፈጠራ በቀውስ ጊዜ በሚል ርእስ ውይይት እያደረገ ነዉ፡፡
የውይይቱ ታዳሚዎች ዶክተር ታምራት ሃይሌ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሰልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የታሪክ ምሁር የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የአእምሮ ሃኪሞች የሆኑት ዶክተር ቢኒያም ወርቁ እና ዶክተር ባርኮት ሚልኪያስ ናቸው።
በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለዉ ውይይት ወረርሽኞች ሲከሰቱ የሚያስከትሉትን ሁለንተናዊ ቀውስ አብራርተዋል
በዓለም ላይ ወረርሽኞች ሲከሰቱ የስነ ልቦና ጫና፣ ሞትን የሚያስከትል በመሆኑ ጭንቀትና ፍርሃት እንዲሁም ማህበራዊ መስተጋብሮችን በማስተጓጎል ፈታኝ መሆኑ ተመልክቷል።ምሁራኑ እንዳነሱት አሁን የተከሰተውን የኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ለመከላከል አዲስ አስተሳሰቦችን ማጎልበት እንደሚገባ ተገልጿል::
በመከላከል ሂደቱ በተለይ ማስክ መጠቀም፣ ማህበራዊ ርቀትና የንፅህና አጠባበቅ ባህል ሆኖ በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ማዘውተርና በተለይ ደግሞ የሰዎችን ጤና እና ስነ ልቦና የሚጎዱ ሱሶችን ማስወገድ እንደሚገባ ተመለክቷል።ዉይይቱም ቀጥሏል