loading
አዲስ አበባ ከ 5 ዓመታት በኋላ የመሶብ ቅርፅ ያለው ባለሰባ ፎቅ ህንፃ ይኖራታል ተባለ

አዲስ አበባ ከ 5 ዓመታት በኋላ የመሶብ ቅርፅ ያለው ባለሰባ ፎቅ ህንፃ ይኖራታል ተባለ

ከ5-6 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ ውስጥ ይገነባል በተባለው ይህ ህንጻ የመሶብ ቅርፅ የያዘበት ምክንያት የአብሮነት፣ የመሰባሰብ፣ የጋራ ደስታና ቃልኪዳን ምሳሌ እንዲሆን ታስቦ ነው ተብሏል።

በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገዛሀኝ አባተ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ህንፃው ባለ 70 ፎቅ ሲሆን 250 ሜትር ከፍታ ይኖረዋል።

ለግንባታው ከ50 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ የሚፈልግ ሲሆን ህንጻው ብቻውን በ20 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያርፋል ተብሏል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ባህላዊና ዘመናዊ ሆቴሎች፣ የገበያ ማዕከል፣ ሁሉንም ክልሎች የሚወክል የባህል ማዕከል፣ የጎልፍ ሜዳ፣ ልዩ ልዩ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ ቢሮ እንዲሁም የቱሪዝምና ሆቴል ዘርፍ ማሰልጠኛ ማዕከል እንደሚኖረው አቶ ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡

ህንጻውን ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት የተጀመረ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገበት ነው።

ህንፃው ሲጠናቀቅ ለመዲናችንና ለሀገራችን ልዩ ድምቀት፣ ባህላዊ እሴቶቻችንን በመግለጽ በማስተዋወቅ ገጽታን በመገንባት ለቱሪዝም እድገት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው የሚል እምነት እንዳለው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ህንጻው የሚገነባበት ስፍራና የሚጠይቀውን ወጪ በተመለከተ ሚኒስቴሩ ወደፊት መግለጫ እንደሚሰጥበት ተነግሯል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *