አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 ኮቪድ 19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን 5 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ አዮዳ አክስዮን የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ድጋፍ አደረገ፡፡
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 ኮቪድ 19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን 5 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ አዮዳ አክስዮን የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ድጋፍ አደረገ፡፡ድጋፉ የተደረገዉ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሰላም ሚኒስቴር ፣ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ፣ ለወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሲሆን የኮቮድ 19 ወረርሽኝን ለመ ከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያዎ ቁሳቁሶች በተለያዮ ማዕከላት ለሚገኙ ህሙማን የመተንፈሻ መሳሪያንና ማረፊያ አልጋንና ያካተተ ነዉ ፡፡
ድንኳን ፣ ማቀዝቀዛና የዉሃ ማጠራቀሚያ ታንከሮች ደግሞ በመተማና በደዋ ለሚገኙ የድንበር መቆጣጠሪያ ኬላዎች የለይቶ ማከሚያ ማዕከላት በቁሳቁስ ለማሟላት ይዉላሉ ተብሏል፡፡የኮቪድ 19 ወረርሽ መከሰቱን ተከትሎ ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በመመደብ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰራ እንደነበርና ከ50 ለሚበልጡ የጤና ተቋማት የኮቪድ 19 መከላከያ ቁሳቁሶችንና እንዲሁም ፕሮግራሙ በሚካሄድባቸዉ አካባቢዎች ግንዛቤ ሲሰጥ እንደነበር ያስታወሱት የግብረ ሰናይ ድርጅቱ ም/ዋና ዳሬክተር በዋናነት ህፃናት ፣ ሴቶችና ወጣቶች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
መሰረቱን እስፔን ያደረገዉ አዮዳ ኢን አክሲዮ ዓለም አቀፍ ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለዉን ተፅዕኖ በመረዳትና የመከላከል ተግባሩ ለመንግሰት ብቻ የሚተዉ አለመሆኑን በመገንዘብ ድርጅቱ ስለሰጠዉ ፈጣን ምላሽ አመስግነዉ ድጋፉ በድንበር አካባቢ ያሉትን ሰዎች በሟቋቋምና እንደ ሀገር የመመርመር አቅማችንን ለማሳደግና ስራዎች በጥንካሬ እንዲቀጥሉ ለማድረግ ያስችላል ያሉት ድጋፉን የተረከቡት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬ ዓለም ሽባባዉ ናቸዉ ፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በማህበረሰብ ዉስጥ 95 በመቶ እንደመሰራጨቱ በኦሮሚያ ክልል ሆነ በወላይታ አካባቢ መስፋፋቱን እንደቀጠለ መሆኑንና በክልል አካባቢ ሰዎች ስለ ቫይረሱ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉና የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባሩ እንዲዳብር እንደሚያደርግ ገልፀዉ ያመሰገኑት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊና ፣ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ ናቸዉ ፡፡የተለያዮ ግብረሰናይ ድርጅቶች ፣ ባለሀብቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰዉን ተፅዕኖ በመረዳት ድጋፍ ማድረጋቸዉን እንዲቀጥሉ በመድረኩ ጥሪ ተላልፏል ፡፡