loading
አይ ኤም ኤፍ ኬንያ ብድር አብዝታለች አለ

አይ ኤም ኤፍ ኬንያ ብድር አብዝታለች አለ

 

አርትስ 22/02/2011

የኬያ የመንግስት ብድር መጠን ከጠቅላላ የሃገር ውስጥ ምርት 63 ነጥብ 2 በመቶ መሸፈኑን አለምቀአፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ይፋ አደረገ።

ሃገሪቱ ሃገሪቱ የዕዳ መጠኗ አስጊ ለመባል የደረሰ ባይሆንም ብድር ግን አብዝታለች ብሏል።

ተቋሙ በቅርቡ ይፋ ባደረገው የኬያ የዕዳ ስጋት ዳሰሳ ሪፖርት ላይ እንደገለጸው የምስራቅ አፍሪካ ጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ኬንያ የዕዳ ስጋቷ መካከለኛ የሚባል ቢሆንም የመንግስት ተበዳሪነት መጠን ግን በጥቂት ፐርሰንት ብቻ ነው ዝቅ ያለው።

የሃገሪቱ የብድር መጠን ከፍ ያለው ከመሰረተ ልማት ዝርጋታ ፕሮጀክቶች ጋ በተያያዘ መሆኑንም ጠቁሟል።

እንደተቋሙ ሪፖርት ሞዛምቢክ ፣ጋና ፣ዚምባብዌ እና ሱዳን  ከፍተኛ የብድር ጫና ካለባቸው የአፍሪካ ሃገራት ተርታ ተመድበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *