loading
አንጎላ ሙስናን ለመዋጋት የተባበሩት መንግስታት ይርዳኝ እያለች ነው

አንጎላ ሙስናን ለመዋጋት የተባበሩት መንግስታት ይርዳኝ እያለች ነው

አርትስ 20/02.2018

የሃገሪቱ ሃብት ተመዝብሮ  በውጭ ሃገራት ተከማችቷል የሚሉት የአንጎላ ባለስልጣናት ሙስናን ለመዋጋት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዲረዳቸው መማጸናቸውን አምነዋል።

ጆርናል ዲ አንጎላ የተባለውን የአንጎላ ጋዜጣ ጠቅሶ ዘ ኢስት አፍሪካን እንደዘገበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዚህ ቀደም ድንበር ዘለል ሙስናን ለመከታተል የተቋቋመውን የሃገሪቱን ጠቅላይ ዐቃቢህግ ቢሮ ሲደግፍ ነበር።

አሁንም ተዘርፎ በውጭ ሃገር የተከማቸ ሃብቴን ለማስመለስ የድርጅቱ ድጋፍ ያስፈልገኛል እያለች ነው አንጎላ  ።

የአንጎላ ብሄራዊ መጠባበቂያ ባንክ ገዢ የሆኑት ሚስተር ጆሴ ዴ ሊማ ማሳኖ እንዳረጋገጡት ከ30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚሆን የአንጎላ ሃብት በውጭ ሃገራት ተከማችቷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማኑኤል አውግስቶ ደግሞ ባለፈው ወር ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው የተሰረቀውን የአንጎላን  ሃብት ለማስመለስ ድጋፍ መጠየቃቸውንአረጋግጠዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *