አንግሊዝ በኮቪድ-19 ብዙ ዜጎች ከሞቱባቸው የአውሮፓ ሀገራት ቀዳሚ ሆነች::
አዲስ አበባ፣ ህዳር 03፣ 2013 አንግሊዝ በኮቪድ-19 ብዙ ዜጎች ከሞቱባቸው የአውሮፓ ሀገራት ቀዳሚ ሆነች:: በመላው ዓለም ዳግም ያገረሸው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከአውሮፓ ሀገራት በተለይ እንግሊዝን ክፉኛ እያጠቃት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው በንግሊዝ በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ስድስት መቶ የሚጠጉ ሰዎ በቫይረሱ ሳቢያ ህይዎታቸው አልፏል፡፡
ይህም በሀገሪቱ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ በላይ እንዲሆን አድርጎታል ነው የተባለው፡፡ በዚህም የተነሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጂንሰን ተነስቶ የነበረው የእንቅስቃሴ እቀባ ዳግም ተግባራዊ እንዲሆን መንግስታቸው አዟል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቫይረሱ ስርጨት ባለሙያዎቻችን ከሰጡን የትንበያ መረጃ በከፋ ሁኔታ እየተባባሰ ነው ብለዋል፡፡
አሁን በእንግሊዝ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት የሚሰጡት የህክምና ተቋማት ች ሲሆኑ ምግብ ቤቶች ደንበኞቻቸው በሬስቶራንት ወስጥ ተቀምጠው እንዲመገቡ ሳይሆን አስጠቅልለው ወደቤታቸው እንዲወስዱ ነው የሚያደርጉት፡፡ ይሁንና በእንግሊዝ ትምህርት ቤቶችን አሁንም ክፍት በመሆናቸው ክፍትየቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ውጤታማ ላይሆን ይችላል ተብሏል፡፡