loading
አቶ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አርትስ 08/04/2011

የክልሉ ምክር ቤቱ 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ሲያካሄድ አቶ አወል አርባን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

አቶ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ለመተግበር የሚያስችል የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በተዘጋጀ አዋጅላይ ተወያይቶ አጽድቆታል።

ምክር ቤቱ በቀጣይም አፈ ጉባኤውን በመምረጥ በርዕሰ መስተዳድሩ የሚቀርቡ የካቢኔ አባላትን ሹመት እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ኤፍ ቢ ሲ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *