አሰልጣኝ ሥዩም አባተ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አርትስ 01/02/2011
አሰልጣኝ ሥዩም አባተ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ አሰልጣኞች አንዱ ነበሩ።
አሰልጣኝ ሥዩም በተጫዋችነት ዘመናቸው ለቅዱስ ጊዮርጊስ እና ለብሔራዊ ቡድን የተጫወቱ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮጵያ መድን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካሰለጠኗቸው ቡድኖች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
አሰልጣኙ ላለፉት ወራት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር ሆስፒታሎች ከፍተኛ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደነበር የሚታወስ ነው።
የቀብር ስነ ስርዓታቸው በነገው ዕለት (ዓርብ ጥቅምት 2 ቀን 2011) ሳሪስ በሚገኘው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ሳሪስ አቦ) ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 09:00 ይፈጸማል።
አርትስ በአሰልጣኝ ሥዩም አባተ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡
ምንጭ:- ሶከር ኢትዮጵያ