loading
አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ከ27 አመታት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ገባች::
አርቲስ አለም ፀሐይ ወዳጆ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የጥበብ አፍቃሪዎችና የቀድሞ የስራ ባልደረቦቿ አቀባበል አድርገውላታል፡፡
በተለያዩ የጥበብ ስራዎች የምትታወቀው አርቲስት አለምፀሀይ ወዳጆ ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ በርከት ያሉ የዘፈን ግጥሞቿ በታዋቂ አቀንቃኞች ተዘፍኗል።
ከጥበብ ተልይቼ መኖር አልችልም የምትለው አርቲስቷ በአሜሪካን ጣይቱ የተሰኘ የጥበብ ማዕከል መስርታ የግጥም ምሽቶችን ድራማዎችንም በማዘጋጀት የጥበብ ስራዋን ያለዕረፍት ስትከውን ለ2 አስርት አመታት በላይ ማሳለፏን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በዚህ በጣይቱ የባህል ማዕከል ከ35 በላይ የመድረክ ድራማዎች ከ150 በላይ የግጥም ምሽቶች ማዕከሉ ባለበት ዲሲ አዘጋጅታለች። እነዚህን የጥበብ ሰራዎች በ17 የአሜሪካ ግዛቶችም በመዘዋወር አሳይታለች።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *