አሜሪካ ከ5 ሺ በላይ ጦሯን ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ልታሰፍር ነው
አሜሪካ ከ5 ሺ በላይ ጦሯን ከሜክሲኮ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ ልታሰፍር ነው
አርትስ 20/02/2011
እንደ ፔንታጎን መረጃ ከማዕከላዊ አሜሪካ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በሜክሲኮ ድንበር በኩል ወደ ሀገሪቱ ይገባሉ ፡፡
ለዚህም ነው ሀገሪቱ ድንበሯን በጠንካራ ወታደራዊ ጥበቃ መዝጋት ያስፈለጋት ፡፡
በተለይም በቴክሳስ ፣አሪዞና እና ካሊፎርኒያ ግዛቶች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግ ታውቋል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ጉዳዩን ወረራ ብለው መጥራታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በድንበር አከባቢ ከፍተኛ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ትራምፕ ይህንኑ ለመከላከል ሁለቱን ሃገራት በሚያዋስነው ድንበር ላይ ግምብ ማስገንባት መጀመራቸው ይታወቃል።
በአሁኑ ወቅት ከ2 ሺ በላይ የአሜሪካ ወታደሮች በድንበሩ አካባቢ ሰፍረው ጥበቃ እያካሄዱ መሆኑንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡