loading
አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው ሌላ ክልል እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ ተስፋቸውን ይቁረጡ አለ አዴፓ

አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው ሌላ ክልል እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ ተስፋቸውን ይቁረጡ አለ አዴፓ

የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው  በክልሉ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን በተከሰተው ግጭት ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች እና በደረሰው የንብረት ውድመት አዴፓ ማዘኑን ገልጸዋል፡፡

ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት የክልሉ መንግሥት ሥጋቱን ያውቀው እንደነበር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም ‹‹እንደስጋት በክልሉ የፖለቲካ ኃይሎች ግጭትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምቶች ነበሩን፤ ግን ከገመትነው የፈጠነ ሆኖብናል›› ብለዋል። ይህን ያክል የንብረት እና የሰው ሕይወት ጠፍቷል ለማለት የቴክኒክ ቡድኑ የጥናት ምላሽ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡

አሁን ሕዝቡ በአዴፓ ላይ ከፍተኛ እምነት የጣለበት ወቅት ነው ያሉት አቶ ዮሐንስ ፤ አዴፓ በሕዝቡ አመኔታ ማግኘቱን ተከትሎ ለመነጣጠል የሚፈልጉ ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ በመሆኑ ሕዝቡ ከጎናችን ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ሕዝቡ መራር በሆነው በዚህ ጊዜ አብሮነቱን እንዲያጠናክር የጠየቁት አቶ ዮሐንስ አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው በሌላ ክልል እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ ተስፋቸውን ይቁረጡ፤ ከአጐራባች ክልሎች እስከ ፌዴራል መንግሥት ድረስ ወንጀለኞችን ለመያዝ በጥምረት እየሠራን ነው›› ብለዋል፡፡

በክልሉ መሠል ችግር እንዳይከሰት ብቂ ዝግጅት እንደተደረገም ተናግረዋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *