loading
አልበሽር ወታደሮቻቸውን በመልካም ቃላት እያባበሉ ነው

አልበሽር ወታደሮቻቸውን በመልካም ቃላት እያባበሉ ነው

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር  በአትባራ አቅራቢያ በሚገኘው ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ጦር ሰራዊታችን ይህን መንግስት በሀይል ለመጣል ከሚያሴሩት ጋር ባለማበሩ ላቅ ያለ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልሽር በ30 ዓመት የስልጣን ዘመናቸው እንደ ዘንድሮው ያለ ተቃውሞ ደርሶባቸው አያውቅም፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ከተቃውሞ ሰልፈኞች በኩል ስልጣናቸውን እንዲለቅቁ ግፊት ቢበዛባቸውም  ከመንበራቸው የሚነቀንቃቸው እንደሌለ  አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

የሱዳን የደህንነት ሰዎች ሰልፈኞቹን ለመበተን የተጠቀሙት ሀይል ከአቅም በላይ መሆኑን በርካታ የመብት ተሟጋቾች በተደጋጋሚ እየገለፁ ይገኛሉ፡፡

በሀገር ደረጃ ደግሞ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ አሜሪካ እና ኖርዌይ የሱዳን መንግስት ዜጎች የመናገር  ነፃነታቸውን እንዳይገልፁ መታፈናቸው ሳይበቃ የተገደሉት ሰዎች ጉዳይ ያሳስበናል ብለዋል፡፡

እስካሁን በአመፁ የተሳተፉ  ከ800 በላይ ግለሰቦች በፖሊሶች ተይዘው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የሱዳን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በመንግስት በኩል አመፁን ተከትሎ  የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 19 ነው ቢባልም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች እና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን አሃዙ ከእጥፍ በላይ ነው እያሉ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *