ኔታኒያሁ የመጣው ይምጣ እንጂ ከስልጣኔ አልወርድም እያሉ ነው፡፡
የእሰራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ በውስጥ ፖለቲካቸው ግፊቶች በዝተውባቸዋል፡፡
በሶስት ትላልቅ የሙስና ወንጀሎች ጠርጥሯቸው ፖሊስ ነጋ ጠባ ለምርመራ የሚጠራቸው ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የካቢኔ አባሎቻቸውም አስቸኳይ ምርጫ ካለተካሄደ ብለው እያስጨነቋቸዉ ነው ፡፡
በተለይ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት በጋዛ በፈፀሙት ጥቃት በርካቶች አምባ ገነን ሲሏቸው ከሀማስ ጋር አደረጉት በተባለወ ድርድር ደግሞ ሀገራችንን አስደፈሩ የሚሉ ሰዎች ቁጣቸው ሲገነፍል ታይተዋል፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረትብዎ ውሳኔ ቢያስተላልፍ ከስልጣንዎ የመልቀቅ ሀሳብ አሎት ወይ ተብለው የተጠየቁት ኔታኒያሁ በፍፁም አላደርገውም ብለዋል፡፡
እየቀረበባቸው ያለውን የሙስና ክስ በተደጋጋሚ ያካሄዱት ኔታኒያሁ የእስራኤል ህግ የክስ ሂደቱ የሚታይ ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣኑ እንዲለቅ ስለማይደነግግ ስልጣን ለመልቀቅ የሚያስቸኩል ነገር የለም ብለዋል፡፡
ኔታኒያሁ ይህን ያሉት በብራዚል ተገኝተዉ ከአይሁዳዉያን ቤተሰቦች ጋር ባደረጉት ዉይይት ነዉ፡፡
የፍርድ ቤቱ ጉዳይ ሳይጠናቀቅ እኔ ከስልጣን ብወርድና በመጨረሻ ነፃ ነህ ብባል ለዲሞክራሲ እድገት መልካም አይሆንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስልጣን ላይ ሆነው እስከመጨረሻው ክሳቸውን እንደሚከታተሉ አስታውቀዋል፡፡
ኔታኒያሁ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ብቻቸውን ሳይሆን ከወንድ ልጃችው እና ከባለቤታቸው ጭምር መሆኑ ይታወቃል፡፡