loading
ናይጄርያ ዜጎቿን እናንተ ድምፅ ስጡ አንጂ መጓጓዣውን ለኔ ተውት ብላለች፡፡

ናይጄርያ ዜጎቿን እናንተ ድምፅ ስጡ አንጂ መጓጓዣውን ለኔ ተውት ብላለች፡፡

የናይጄሪያ ነዳጅ አቅራቢዎች  የታክሲና አውቶቡስ ሹፌሮች፣ እንዲሁም የአየር መንገዶች  በመጪው ቅዳሜ በሜካሄደው  ምርጫ ድምፅ ለመስጠት  ከተለያዩ  ቦታዎች  ለሚመጡ   መራጮች  የታሪፍ ቅናሽ ሊያደርጉ ነው፡፡

የድምፅ ሰጪዎች ቁጥር አነስተኛ እንዳይሆን ያሳሰባቸው የሁለቱም ተፎካካሪ ወገኖች  በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ እና ለመምረጥ የተመዘገቡት ነዋሪዎች  እንዳይቸገሩ በማሰብ ነዉ ይህን ያደረጉት፡፡

ፓርቲዎቹ ከምርጫ ጣቢያዎች እስከ መኖሪያቸው ድረስ ለመጓዝ አቅሙ ለማይፈቅድላቸው ነዋሪዎች የትራንስፖርት  ወጪያቸው ላይ ቅናሽ ለማድረግ ስምምነት አድርገዋል፡፡

በመጪው ቅዳሜ የሚደረገው የናይጄርያ ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ 84 ሚሊዮን ሰው  ድምፅ ለመስጠት መመዝገቡን የናይጄርያ  የምርጫ ኮሚሽን  ገልጿል፡፡

የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ  ሊይ መሀመድ  ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት  2 ሚሊዮን አባለት ያሉት  በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰራው  የትራንስፖርት ባለስለጣን  መራጮችን  ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ ቀና ትብብር አሳይቷል፡፡

ነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶችም የነዳጅ ዋጋን ከ 145 ወደ 140 ናኤራ  በሊትር  ዝቅ አድርገዋል ነው ያሉት፡፡

አፍሪካ ኒውስ በዘገባው ሁለት አየር መንገዶችም ከተለያዩ  ሀገራት ድምፅ ለመስጠት  ለሚንቀሳቀሱ ዜጎች  ድምፅ መስጫ ካርዶቻቸውን ብቻ በማየት ቅናሽ ማድረጉን አስነብቧል፡፡

የናይጄርያው ፕሪዝዳንት ሙሀማዱ ቡሃሪ  የሀገሪቱን የነዳጅ ሃብት ከሙሰኞች እጅ ለማውጣት እና በሀብታም እና ደሀ መሀከል ያለውን ልዩነትት ለማጥፋት የሚለውን አቋማቸውን አሁንም ለቅስቀሳ ተጠቅመውበታል፡፡

ተፎካካሪያቸው  አቲኩ አቡበከር ደግሞ በናይጄርያ ያለውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቅረፍ እንደሚሰሩ ተናገረዋል፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *