loading
ናይጀሪያ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች ምርጫየን ሊታዘቡ ይችላሉ ብላለች፡፡

ናይጀሪያ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች ምርጫየን ሊታዘቡ ይችላሉ ብላለች፡፡

የፕሬዝዳንት ሙሀማዱ ቡሀሪ ረዳት ናስር አል ሩፋይ በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚሞክር ማንኛውም አካል ወደ መጣበት ይመለሳል የሚል ማጠንቀቂያ በሰጡ ማግስት ነው አቡጃ ይህን ያለችው፡፡

አል ሩፋይ መግለጫውን በሰጡበት ወቅት እኛ ለሀገራችን ምን መስራት እንዳለብን ሊያስተምረን የሚመጣ ሰው የለም ነው ያሉት፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን ምርጫውን የመታዘብ ተግባሩን ለማከናወን ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡

ታዛቢ ቡድኑ በመላ ሀገሪቱ ስራውን በሚያከናውንበት ወቅት የፀጥታው ሁኔታ እንደሚያሳስበውም ይፋ አድርጓል፡፡

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር የካቲት 16 የሚካሄደው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሙሀማዱ ቡሀሪ እና የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት አቱኩ አቡበከር በዋናነት የሚፋለሙበት ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ዓመት ፕሬዝዳንት ቡሀሪ እና ተቀናቃኛቸው አቡበከር ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ያላቸውን ቁርጠኝነት በፊርማ ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *