ኒው ዚላንድ ከሀዘኗ መፅናናት ተስኗታል፡፡
ኒው ዚላንድ ከሀዘኗ መፅናናት ተስኗታል፡፡
በዚህች ሀገር የተከሰተው በታሪኳ ታይቶ የማያውቀው የጅምላ ግድያ የብዙዎቹን ልብ በመሪር ሀዘን ሰብሯል፡፡
ይህ በሙስሊሞች ላይ የተፈፀመው ግድያ ሳያንስ የሟቾቹ የቀብር ስነስርዓት መዘግየቱ ለቤተሰቦቻቸው ሌላ ተጨማሪ ሀዘን ሆኖባቸዋል፡፡
በሙስሊሞች ደንብ መሰረት አንድ ሰው በሞተ በ24 ሰዓት ውስጥ መቀበር አለበት፡፡ ይሁን እንጂ ፖሊስ የሟቾቹን ማንነት ለይቸ አላጠናቀቅኩም በማለቱ ምክንያት እስካሁን ቤተሰቦቻቸውን መቅበር አልቻሉም፡፡
ፖሊስ በበኩሉ የእኛ ቀዳሚ ተግባር ስህተት እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ማድረግ በመሆኑ የተጎጂ ቤተሰቦች እንዲታገሱን እንጠይቃለን ብሏል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው የኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን የሟቾቹን ማንነት የመለየት ስራው ቢበዛ ከረቡእ አያልፍም ብለዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ