loading
ቻይና የአለም ረጅሙን ባህር አቋራጭ ድልድይ ገነባች

አርትስ 13/02/2011

ሃገሪቱ አስር አመታት የወሰደውና ከሆንግ ኮንግ ጋ የሚያገናኛትን 55 ኪሎሜትር ርዝመት ያለውን ድልድይ አጠናቃ አስመርቃለች።

ድልድዩን መርቀው ስራ ያስጀመሩት የቻይና ፕሬዚዳንት ዢን ፒንግ ናቸው። የድልድዩ  መገንባት በርካታ  ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል።

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህ የዓለም ረጅሙ ድልድይ ለግንባታ 20 ቢሊዮን ዶላር የፈጀ ሲሆን ከታቀደለት ጊዜ እና በጀት የበለጠ ፈጅቷል ተብሏል።

ድልድዩ የቻይና ማምረቻ ማዕከል በሆነው ፐርል ሪቨር ዴልታ በሚባለው አካባቢ ሲደርስ መርከቦች ያለችግር እንዲተላለፉ ለማስቻል ተብሎ ከባህር በታች በተቆፈረ ዋሻ ውስጥ እንዲያልፍ ተደርጓል።

ይህ ድልድይ በርካታ ሰዓታትን ይፈጅ የነበረውን ጉዞ ወደ30 ደቂቃ ብቻ አሳጥሮታል።ይህም ቻይና ሁለቱን አካባቢዎች የኢኮኖሚ ጥምረት ለመፍጠር ያላትን ግብ ያሳካል ተብሎ ይጠበቃል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *