ቻይና እስካለፈው የፈረንጆች 2018 ድረስ በኢትዮጵያ ላይ የተጠራቀመውን የብድር ወለድ ሙሉ በሙሉ ሰረዘች
ቻይና እስካለፈው የፈረንጆች 2018 ድረስ በኢትዮጵያ ላይ የተጠራቀመውን የብድር ወለድ ሙሉ በሙሉ ሰረዘች።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቻይና የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቤጂንግ እንደሚገኙ ይታወቃል። በጉብኝታቸው ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄዳቸው ይታወቃል።
የእዳ ስረዛው ይፋ የሆነውም ይህንኑ ውይይት ተከትሎ ነው ተብሏል።
አንዳንድ ምንጮች እንደሚጠቅሱት ኢትዮጵያ 20 ቢሊዮን ዶላር የቻይና እዳ አለባት።
ዝርዝሩን እንደደረሰን በምሽት ዜና እወጃችን ይዘን እንቀርባለን።