ትራምፕ የጠፋዉን ጋዜጠኛ ጉዳይ በቸልተኝነት አልመለከተዉም አሉ
የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናዉ ዕለት “ ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የጠፋዉን ጋዜኛ ጀማል ሃሾጊ ጉዳይ ቸል አላልኩትም፤ ከሳዉድ አረቢያና ከቱርክ ባለስልጣናት ጋር እንዲመክሩ የተላኩትን የማይክ ፖምፒዮን ሙሉ ሪፖርት ነዉ የምጠብቀዉ” ብለዋል፡፡
ሮይተርስ አንዳንድ የቱርክ የመረጃ ምንጮች ነግረዉኛል ሲል እንደዘገበዉ ጋዜጠኛዉ በሳዉዲ ኤጀንቶች በቆንስላዉ ጊቢ መገደሉን የሚያሳይ የድምፅ ቅጂ ያሳያል ብሏል፡፡
የዋሺንግተን ፖስት አምደኛ በጥልቅ ትንታኔዉ የሳዑዲ አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን በፈረንጆቹ ኦክቶበር 2/2018 ዓ.ም ሃሾጊን ገድለዉ አስከሬኑን አስወግደዉታል ሲል መዘገቡ አሳምኖናል ሲሉ የቱርክ ባለስልጣናት ገልፀዋል ፡፡