loading
ታላላቅ ቡድኖች ወደ አራተኛው ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች አልፈዋል

ታላላቅ ቡድኖች ወደ አራተኛው ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታዎች አልፈዋል

የሶስተኛው ዙር የኤፍ ኤ ካፕ ግጥሚያዎች በትናንትናው ዕለት በርከት ብለው ተካሂደዋል፤ ዛሬም ጥቂት የማይባሉ ጨዋታዎች ቀጥለው ይከናወናሉ፡፡
በኦልትራፎርድ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ሬዲንግ ጋር ተጫውቶ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ድል አድርጎ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል፡፡ አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር አምስተኛ ተከታታይ ድሉን እንዲያስመዘግብ ያገዙትን ግቦች ከመረብ ያገናኙት ደግሞ ስፔናዊው የሃን ማታ በፍፁም ቅጣት ምትና ሮሜሉ ሉካኩ በጨዋታ ነው፡፡ በጨዋታው ፍሬድ ከጨዋታ ውጭ ሁኖ እያለ አርቢትር ስቱዋርት አትዌል ፍፁም ቅጣት መስጠታቸው በቫር ላይ ብዥታን ፈጥሯል፡፡
ቼልሲ ደግሞ በሜዳው ስታንፎርድ ብሪጅ ኖቲንግሃም ፎረስትን አስተናግዶ በአልቫሮ ሞራታ ግቦች 2 ለ 0 በመርታት ወደ አራተኛው ዙር የተቀላቀለ ሌላኛው ቡድን ሁኗል፡፡ ለሞራታ ሁለት ግቦች መቆጠር ምክንያት የሆነው ደግሞ ሁድሰን ኦዶይ ነው፡፡
አርሰናል ወደ ብላክ ፑል አቅንቶ በወጣቱ ጆ ዊሎክ ሁለት ግቦች እና ኢዎቢ ተጨማሪ ግብ 3 ለ 0 አሸንፎ ዙሩን ተሻግሯል፡፡
ኢቨርተን በጉዲሰን ፓርክ ሊንከልን ሲቲን በሎክማን እና ቤርናርድ ግቦች 2 ለ 1 ረትቷል፡፡ ከተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች መካከል ብራይተን በርንማውዝን 3 ለ 1፣ ዌስት ሃም በርሚንግሃምን 2 ለ 0፣ በርንሌ በርንስሌይን፣ ክሪስታል ፓላስ ግሪምስቢ ታውንን፣ ብሪስቶል ሲቲ ሀደርስፊልድን ጊሊንግሃም ካርዲፍን በተመሳሳይ 1 ለ 0 ረትተው ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፉ፤ ኒውካስትል ከብላክበርን 1 ለ 1 እንዲሁም ደርቢ ከሳውዛምፕተን 2 ለ 2 ተለያይተዋል፤ የመልስ ግጥሚያም ያደርጋሉ፡፡
ዛሬ በ11፡00 ኢቲሃድ ላይ ማንችስተር ሲቲ ከ ሮዘርሃም፣ ፉልሃም ከ ኦልድሃም፣ ወኪንግ ከ ዋትፎርድ ሲገናኙ፤ 1፡30 ሲል ኒውፖርት ከ ሌስተር ሲቲ ይፋለማሉ፤ ነገ ደግሞ ወልቭስ ምሽት 4፡45 ላይ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል፡፡
የአራተኛ ዙር ጨዋታዎች ዕጣ ድልድል ከወልቭስ እና ሊቨርፑል ጨዋታ በኋላ ይፋ ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *