ተጠባቂው የኢል ክላኮ ፍልሚያ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
ተጠባቂው የኢል ክላኮ ፍልሚያ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
በስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ፤ በኢል ክላሲኮ ደርቢ ትናንት ምሽት ባርሴሎና ከ ሪያል ማድሪድ በካምፕ ኑ ተገናኝተው ሳይሸናነፉ በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ጨዋታው በተጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እንግዳዎቹ ሎስ ብላንኮስ ከካሪም ቤንዜማ የተሻገረችውን ኳስ ሉካስ ቫዝኪውዝ በ6ኛው ደቂቃ ወደ ግብነት ቀይሮ ቡድኑን መሪ አደረገ፤ በመጀመሪያው አሰላለፍ ያለ ሜሲ ወደ ሜዳ የገባው ባርሳ በብራዚላዊው ማልኮም አማካኝነት ከዕረፍት መልስ ኳስን ከመረብ በማገናኘት የካታላኑን ቡድን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡
ባርሳ በጨዋታው አሸናፊ ለመሆን ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካላትም፡፡
በጉዳት ምክንያት በመጀመሪያው አሰላለፍ ያልተካተተው ሊዮኔል ሜሲ በ63ኛው ደቂቃ በኮቲንሆ ተቀይሮ ቢገባም ቡድኑን ግን ወደ አሸናፊነት መመለስ አልቻለም፡፡
የትናንት ምሽቱ ኢል ክላሲኮ በ25 ቀናት ውስጥ ከሚከናወኑ ሶስት የደርቢ ግጥሚያዎች አንዱ ሲሆን ሁለተኛውና የኮፓ ዴል ሬይ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ፍልሚያ ከ20 ቀናት በኋላ በሳንቲያጎ ቤርናቤው ይከናወናለል፡፡
ዛሬ ምሽት 5፡00 ሌላኛው የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታ በሪያል ቤቲስ እና ቫሌንሲያ መካከል እስታዲዮ ቤኒቶ ቪያማሪን ላይ ይገናኛሉ፡፡