loading
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ምዕራብ ወለጋ አዋሳኝ መንገድ ላይ በተቀበረ ፈንጂ 10 ሰዎች ሞቱ

አርትስ 10/04/2011

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ምዕራብ ወለጋ አዋሳኝ አካባቢ ልዩ ስሙ ቶንጎ ጉሬ በሚባል ስፍራ መንገድ ላይ የተቀበረ ፈንጂ ተሳፋሪ ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ሚኒባስ ተረግጦ በመፈንዳቱ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡
ሚኒባሱ በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ ልዩ ስሙ ጉሬ የስደተኞች ካምፕ አካባቢ እየተጓዘ ሳለ ነው በጠጠር መንገድ ላይ የተቀበረው ፈንጂ ፈንድቶ አደጋውን ያደረሰው፡፡
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ አስዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከማል እንድሪስ እንደተናገሩት በአደጋው የ10ሰዎች ህይወት አልፏል። የሁለቱ ሰዎች ህይወት ሆስፒታል ከደረሱ በኃላ ነው ያለፈው፡፡
ፈንጂው በማን እና ለምን እንደተጠመደ የፀጥታ ሀይሎች እያጣሩ መሆኑንም ሃላፊው ገልፀዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *