ቡተፍሊካ ከስልጣናቸው የሚወርዱበትን ቀነ ገደብ ተናገሩ፡፡
ቡተፍሊካ ከልጣናቸው የሚወርዱበትን ቀነ ገደብ ተናገሩ፡፡
ህዝባዊ አመፅ አላስቆም አላስቀምጥ ያላቸው የአልጀሪያው ፕሬዝዳንት አብደልአዚዝ ቡተፍሊካ ከመንበረ ስልጣናቸው የሚለቁበት ቀን በፈረንጆቹ ከሚያዚያ 28 በፊት እንደሆነ ተሰምቷል፡፡
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ መረጃውን ከፕሬዝዳንቱ ቢሮ አገኘሁት ብሎ እንደዘገበው ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የመንግስ ተቋማት ስራቸውን በነበሩበት ይቀጥላሉ፡፡
ቡተፍሊካ ለአምስተኛ ጊዜ በምርጫ እወዳደራለሁ ብለው መናገራቸውን ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የተቀሰቀሰው አመፅ ሁለት ሶስት ጊዜ ሀሳባቸውን አስቀይሯቸዋል፡፡
የሀገሪቱ መከላከለያ ኢታማጆር ሹም ፕሬዝዳንቱ በጤና እክል ሳቢያ ስራቸውን መቀጠል ስለማይችሉ ይውረዱ የሚል ጥያቄ ከአንድም ሁለቴ ማቅረባቸውም የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡
በጨረሻ ግን ይህ ወር ከመጠናቀቁ ቀደም ብለው ስልጣናቸውን መልቀቃቸው እውን እንደሚሆን ከራሳቸው ከፕሬዝዳንቱ ቢሮ የወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡
ለተቃውሞ ሰልፍ ሰርክ አደባባይ የሚወጡ አልጀሪያዊያን ግን ጥያቄያቸው ቡተፍሊካ ከስልጣን ይውረዱ ብቻ ሳይሆን ያረጀ ያፈጀ የፖለቲካ ሲስተም በሰለጠነ እና በአዲስ አስተሳሰብ ይቀየር የሚል ነው፡፡
አንዳንዶች ቡተፍሊካ እስካሁን በስልጣናቸው የቆዩት በሳቸው ፍላጎት ብቻ ሳይሆን በነገሩ የጦር አለቆች እና ፖለቲካውን በመዘወር የሚጠረጠሩ ቱጃሮች እጅ ስላለበት ነው ይላሉ፡፡
መንገሻ ዓለሙ