loading
ቡሃሪ ለሁለተኛ ዙር የምርጫ ቅስቀሳቸውን በይፋ ጀምረዋል

ቡሃሪ ለሁለተኛ ዙር የምርጫ ቅስቀሳቸውን በይፋ ጀምረዋል፡፡

የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ሙሀማዱ ቡሀሪ በሰሜናዊ ናይጀሪያ በምትገኘው ትልቋ የኢኮኖሚ ከተማ ካኖ በአስር ሺህዎች በሚቆጠሩት ደጋፊዎቻቸው ፊት ቀርበው ነው ለዳግም ምርጫ መጥቻለሁ ተዘጋጁ ያሉት፡፡

ቡሀሪ በተደጋጋሚ በህመም ምክንያት ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር መመላለስ ማብዛታቸው እና ከስራ የሚርቁበት ጊዜ በመብዛቱ ተፎካካሪዎቻቸው ለስራው ብቁ አይደሉም በማለት ይከራከራሉ፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ከኒጀር የመጡ የአውራጃ አስተዳዳሪዎች በስነ ስርዓቱ ላይ መገኘታቸውን ተቃውሟ፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ፕሬዝዳንቱ ከአሁኑ የምርጫውን ውጤት በጎረቤት ወዳጆቻቸው ድጋፍ ለማስቀየር   እየተዘጋጁ ነው የሚል ነው፡፡

ቡሀሪ ለሁለተኛ ጊዜ ከመረጣችሁኝ በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ እንዲሁም ኢኮኖሚያችን እንዲያድግ ተግቼ እሰራለሁ ማለታቸውም ተሰምቷል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በመጀመሪያው ዙር የስልጣን ቆይታቸው ሙስንን እና ቦኩ ሀራም የተባለውን ታጣቂ ቡድን ለማጥፋት የገቡትን ቃል አልፈፀሙም ተብለው ይወቀሳሉ፡፡

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *