በፈረንሳይ ሊግ አንድ ፒ.ኤስ.ጂ በድጋሚ ነጥብ ጥሏል
በፈረንሳይ ሊግ አንድ ፒ.ኤስ.ጂ በድጋሚ ነጥብ ጥሏል
አርትስ ስፖርት 27/03/2011
በ16ኛ ሳምንት የፈረንሳይ ሊግ አንድ ጨዋታዎች ትናንት በርካታ ጨዋታዎች ተከናውነዋል፤ በምሽቱ የሊጉ መሪ ፓሪስ ኤንድ ጀርሜን ከሜዳው ውጭ ከ ስትራስበርግ ጋር ተጫውቶ በአንድ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ ኬኒ ላላ ባለሜዳዎቹን በፍፁም ቅጣት ምት ቀዳሚ ማድረግ ቢችልም፤ ኢዲንሰን ካቫኒ በ71 ደቂቃ በፍፁም ቅጣት ምት አቻ አድርጓል፡፡ በ15ኛው ሳምንት የሊጉ መርሀግብር ፒ.ኤስ.ጂ ባለፈው እሁድ የአሸናፊነት ጉዞው በ2 አቻ ውጤት በቦርዶ መገታቱ ይታወሳል፡፡
ሊዮን በሬን የ2 ለ 0 ሽንፈት ሲያስተናድ፣ ኒም ኮን፣ ዲዦ ገንጎን በተመሳሳይ 2 ለ 1 ረትተዋ፤ ኖንት ማርሴን፣ ቦርዶ ሴንት ኢቴንን ደግሞ በተመሳሳይ የ3 ለ 2 ድል ተቀዳጅተዋል፡፡
በቴሪ ኦንሪ የሚሰለጥው ሞናኮ ከሜዳው ውጭ በራዳሚል ፋልካኦ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምት ጎሎች አሜየን 2 ለ 0 በመርታት የድል መንገድን አስቀጥሏል፡፡ ሊል ሞንፔሌን 1 ለ 0፣ ኒስ ከ ኦንዤ ያለግብ አቻ ተለይይተዋል፡፡
ሊጉን ፓሪስ ኤን ጀሪመን በ44 ነጥብ ሲመራ ሊል በ30 ይከተላል፤ ሞንፔሌ በ29 ሶስተኛ፣ ሊዮን በ28 አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡