በጣሊያ ሱፐር ኮፓ ዩቬንቱስ ባለድል ሁኗል
በጣሊያ ሱፐር ኮፓ ዩቬንቱስ ባለድል ሁኗል
የጣሊያን የአሸናፊዎች አሸናፊ (ሱፐር ኮፓ) ጨዋታ በሁለቱ የጣሊያን እግር ኳስ ስኬታማ ክለቦች ዩቬንቱስ እና ኤሲ ሚላን መካከል ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ላይ ተካሂዷል፡፡
በትናንት ምሽቱ ጨዋታ ቢያንኮኔሪዎቹ በሁለተኛው አጋማሽ ከሚራለም ፒያኒች የተሻገረችውን ኳስ ፖርቱጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ አንድ ጎል 1 ለ 0 በማሸነፍ 8ኛ የሱፐር ኮፓ ዋንጫቸውን ወደ ካዝናቸው ቀላቅለዋል፡፡
ሮናልዶም ከአሮጊቷ ጋር የመጀመሪያ ዋንጫውን ማሳካት ችሏል፤ በሁሉም ውድድሮች ደግሞ 16ኛ ጎሉን ከመረብ አገናኝቷል፡፡
ፓትሪክ ኩትሮኔ በአግዳሚ ብረቱ የተመለሰበት መንገድ ሮሶኔሪዎቹን የሚያስቆጭ ሲሆን የአይቮሪያዊ አማካይ ፍራንክ ኬሲ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበት ቡድኑን ጎድቶታል፡፡
በጥር የዝውውር መስኮት ስሙ በሰፊው ከቼልሲ የተያያዘው ጎንዛሎ ሂግዌን በጨዋታው በአሰልጣኝ ጅናሮ ጋቱሶ ተቀይሮ ነው መግባት የቻለው፡፡
አሰልጣኙ ግን የሂግዌን በመጀመሪያው አሰላለፍ ውስጥ አለመካተት ከዝውውሩ ጋር የተገናኘ ምንም ነገር የለም ህመም ላይ ስለነበረ ነው ብሏል፡፡