በግብጽ እስር ቤቶች በጤና ችግር ሳቢያ የሚሞቱ እስረኞች ቁጥር እየጨመረ ነዉ
ምክንያቱ ደግሞ ያልተገባ አያያዝ፣ የህክምናና የመድሀኒት እጥረት መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተናግረዋል፡፡
የእስረኞቹ ጠበቆችም የደንበኞቻቸውን የጤና ሁኔታ ተከታትለው እንዳይመዘግቡና መረጃ እንዳያገኙ እየተደረጉ ነው ይላል የሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ፡፡
በግብጽ የአንድ ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ መሪ የነበሩት አብደል ሞኔም አቡል ፎቱህን የጤና ሁኔታ በማሳያነት ያነሳሉ የመብት ተሟጋቾቹ፡፡
ግለሰቡ በፌስ ቡክ ገጻቸው የእስር ቤቱ አስተዳዳሪዎች ሆስፒታል ሄጄ እንዳልታከም ከልክለውኛል በማለት ጽፈዋል፡፡
በግብጽ እስር ቤቶች ወደ 60ሺ የሚጠጉ ታራሚዎች እንደሚገኙና አብዛኞቹም የሰብዓዊ መብት አያያዛቸው ችግር እንዳለበት ይነገራል፡፡