በጅግጅጋ ከ41 ሺህ በላይ ዶላር ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙ ተገለፀ
በጅግጅጋ ከ41 ሺህ በላይ ዶላር ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙ ተገለፀ
አርትስ 11/04/2011
እንደ ገቢዎች ሚኒስቴር ገለፃ 41 ሺህ 693 የአሜሪካ ዶላር በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች በጅግጅጋ ቅርንጫፍ አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውለዋል ፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በቶጎ ጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ነው፡፡
አቶ ደመላሽ መንግሥት ህገ-ወጥ ደርጊቶችን ለመከላከል ከምንጊዜውም በላይ ጠንክሮ እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ህዝቡም እያደረገ ላለዉ ንቁ ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይ ህገወጦችን በንቃት በመከታተል ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ የበኩሉን ሃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም ኃላፊው ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡