loading
በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች የከንቲባውን ቢሮ አቃጠሉ፡፡

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች የከንቲባውን ቢሮ አቃጠሉ፡፡

ተቃዋሚዎቹ በምስራቃዊ የኮንጎ ግዛት በምትገኘው ቤኒ ከተማ በደረሰ ጥቃት 8 ሰዎች በመገደላቸው ተበሳጭተው ነው ይህን ድርጊት የፈፀሙት ተብሏል፡፡

ነዋሪዎቹ በተደጋጋሚ መንግስት ከሚደርስባቸው ጥቃት እንዲታደጋቸው ቢወተውቱም አሁንም ከመንግስ በኩል የህይዎት ዋስትና እንደሌላቸው ነው የሚናገሩት፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ጥቃቱን ያደረሱት በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው አላይድ ዲሞክራቲክ ፎርስ የተባለው ተቃዋሚ ቡድን አባላት ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥርጣሬ አለ፡፡

አላይድ ዲሞክራቲክ ፎርስ የተባለው ተቃዋሚ ሀይል በኡጋንዳ ድንበር አካባቢ በመትገኘው በማእድን በበለፀገችው ቤኒ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ሀይሎች መካከል ዋነኛው መሆኑ ይነገራል፡፡

ባለፈው ወር ብቻ በዚህ አካባቢ ከ70 በላይ ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል ነው የተባለው፡፡

በዚህ ብስጭት የገባቸው ነዋሪዎች የተባበሩት መንግስታት ቢሮ አካባቢ በመሰባሰብ ተቃውሟቸውን ከመግለፅ አልፈው የከንቲባውን ቢሮ እስከማቃጠል ደርሰዋል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *