በደቡብ ኮሪያ ደራሽ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት 13 ሰዎችን ገደለ::
አዲስ አበባ፣ሐምሌ28፣ 2012 በደቡብ ኮሪያ ደራሽ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት 13 ሰዎችን ገደለ:: በዋና ከተማዋ ሴኡል አቅራቢያ በሚገኙ አካባዎች የተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ከሟቾቹ በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ትተው እንዲፈናቀሉ አድርጓል ነው የተባለው፡፡ አንድ የ60 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 13 ሚሆኑ ሰዎች የገቡበት እንዳልታወቀም አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡
ጎርፉ ከ5 ሺህ ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት እና በሴኡል የሚገኙ ድልድዮችን ጭምር በማጥለቅለቅ ለአደጋ አጋልጧቸዋል፡፡ የሀገሪቱ መንግስት ከ25 ሺህ በላይ የፖሊስ አባላትን በስፍራው በማሰማራት ህይዎት የመታደግና አደጋውን የመቀነስ ስራ እንዲሰሩ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡
ደቡብ ኮሪያ በተፈጥሮ አቀማመጧ ተራራማ ስፍራ ስለሚበዛባት ለጎርፍና ለመሬት ለመሬት መንሸራተት አደጋዎች የመጋለጥ አድሏ ሰፊ መሆኑ ይነገራል፡፡ የቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ሙን ጃይ ኢን የገሪቱ ባለ ስልጣናት ህዝቡን ከተጨማሪ አደጋ እንዲታደጉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል፡፡ የአየር ትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በቀጣዮቹ ቀናትም በሀገሪቱ ከባድ ዝናብ ስለሚጠበቅ አደጋው ተባብሶ እንዳይቀጥል ተሰግቷል፡፡